Fana: At a Speed of Life!

12ኛው የጣና ፎረም መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 12ኛው የጣና ፎረም “የሰላም መንገዶች በአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካዊ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀምሯል።

በመድረኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በአህጉሪቱ ሰላም፣ ደህንነት እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ዙሪያ ምክክር ያደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በመድረኩ እየተቀያየረ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ አፍሪካ የሚኖራትን ሚና በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.