Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች ርክክብን በተመለከተ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ከጥቂት ዓመታት በፊት አጠቃላይ የኢትዮጵያን ስጋት ለመቀነስ እንዲሁም በዓለም ሀገራት ዘንድ የአየር የበላይነትን ለመውስደ የሚደረገውን ሩጫ በመገንዘብ ከሩሲያ መንግሥት ጋር የሱ-35 4ኛ ትውልድ ኤር ክራፍት ስምምነት ፈጽመን ነበር፡፡
👉 ስምምነቱ ጊዜው ደርሶ የመጀሪያው ዴሊቨሪ ስምምነት በ2027 ቢሆንም ከሬዚዳንት ፑቲን ጋር በህንድ በነበረን ቆይታ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያቀርቡልን ባቀረብነው መሰረት የመጀመሪያውን ሱ-35 ተረክበናል፡፡
👉 በመጀመሪያው ዙር 12 የሱ ሶስት ኤርክራፍቶችን እንዲሁም አራት ኤስ 400 የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ትረከባለች፣ እነዚህ አቅሞች ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አላቸው፡፡
👉 በተለያዩ ሀገራት በግጭት ጊዜ ያለው ምስቅልቅል ችግር ከመፈጠሩ በፊት በሰላሙ ጊዜ መደረግ የሚገባውን ዝግጅት ካለማድረግ የሚመጣ ነው፡፡
👉 ኢትዮጵያ በብዙ ጠላት የተከበበች ሀገር ናት፣ ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው፣ የአየር ክልላችን እንዳይደፈር በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
👉 ይህ የምናየው የሱ 35 ኤር ክራፍት በዓለም ላይ ምርጡ የሚባለው የዘመኑን ቴክኖሎጂ የታጠቀ ኤር ክራፍት ነው፤ የአየር እና የምድር ውጊያዎችን ማድረግ ይችላል፡፡
👉 እንዲሁም የክሩዝ ሚሳኤሎችን የማክሼፍ አቅም ያለው ጄት ነው፤ ክሩዝ ሚሳኤሎችን እስከ 200 ኪሎ ሜትር ድረስ መነሻቸውን በማጥናት ማምከን የሚችል ነው፡፡
👉 ይህን የአየር መከላከል አቅም ካልገነባን እንደ ሀገር ህልውናችንን ለማስቀጠል እንቸገራለን፤ በዚህ ምክንያት ሰው ስናሰለጥን ቆይተናል፤ አሁን የታጠቅናቸው ሱ-35ቶች በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የአየር ክልሎች ለመከላከል ያግዛሉ፡፡
👉 በቂ የጦር አቅም ያላቸው ሀገራት በቀላሉ አይደፈሩም፤ ያልተዘጋጀ መንግሥት ውጊያን ይጋብዛል፤ የተዘጋጀ ግን ውጊያን ያስቀራል፤ ከዚህ አንፃር የዛሬው ስምምነት ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡
👉 በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ኢትዮጵያ የሱ- 35 የታጠቀች ብቸኛዋ ሀገር ናት፤ በድሮን ብቻ ሳይሆን በሱ 34 እና 35 የአየር የበላይነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች፡፡
በሚኪያስ አየለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.