Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶቡሶችን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ሀገር በአንድ ጀምበር እና በአንድ ትውልድ አትገነባም፤ ሀገር መገንባት ውስብስብ ሂደት አለው፤
👉 በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ወደ 400 የሚጠጉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ አውቶቡሶች ይገባሉ፤
👉 እነዚህ አውቶቡሶች እስኪገቡ ድረስም ነባር አውቶቡሶችን ወደ ጋዝ የመቀየር ሥራው ይቀጥላል፤
👉 400ዎቹ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት ሲገቡ፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት የአንበሳ አውቶቡሶች ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ይሆናል፤
👉 መጪው ጊዜ ለልጆቻችን እና ለኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪና ብሩህ ነው፤
👉 ጋዝ እናወጣለን ብለን ጋዝ ማውጣት ችለናል፤ መናገር ብቻ ሳይሆን፤ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎችን አልፎ ስራው ተጠናቅቆ ለህዝብ ጥቅም ማዋል የአንድ መንግሥት መለኪያ ነው፤
👉 የምንናገረውን ወደ ተግባር መቀየር የኢትዮጵያ መንግሥት መታወቂያ ነው፤
👉 በአፍሪካም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚናገረውን ይፈጽማል የሚል እሳቤ እየጎላ መጥቷል፤
👉 የትራንስፖርት ወጪ ከቀነስን፤ አሁን በተጀመረው የቤት ፕሮግራም በተቻለ መጠን ቤት ማቅረብ ከቻልን፤ ምግብ ላይ የጀመርነውን ስራ ከሰራን ለውጥ እናመጣለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ፣ ትራንፖርት እና ቤት ሰውን እያሰቃየ መሆኑን ጠቁመው፤ እነዚህ ሦስት ጉዳዮች እየተፈቱ ሲሄዱ ሰዎች ባላቸው ገቢ ልክ የተሻለ ኑሮ የሚያስችል እድል እንደሚያገኙ አመልክተዋል፡፡
👉 የኢትዮጵያ ተስፋ በብዙ መንገድ እየታየ ነው፤ በልማቷ በጣም አመርቂ ውጤቶች እየታዩ ነው፤
👉 ከጥረት፣ ከስራ እና ከትጋት ውጪ የሚገኝ ውጤት የለም፤ በልፋት ብቻ ነው ሀገር የምንቀይረው፤
👉 በጥቂት ዓመታት ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን የነዳጅ ተጠቃሚ አውቶቡሶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ጋዝ እንቀይራለን፤
👉 በቀጣዮቹ ዓመታትም የጋዝ አውቶቡሶችን ቁጥር በየደረጃው በማሳደግ፣ በአዲስ አበባ በነዳጅ የሚሠሩ የከተማ አውቶቡሶችን በሙሉ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር ታቅዷል፤
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.