ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶቡሶችን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- On Oct 30, 2026 16 ሀገር በአንድ ጀምበር እና በአንድ ትውልድ አትገነባም፤ ሀገር መገንባት ውስብስብ ሂደት አለው፤ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ወደ 400 የሚጠጉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ አውቶቡሶች ይገባሉ፤ እነዚህ አውቶቡሶች እስኪገቡ ድረስም ነባር አውቶቡሶችን ወደ ጋዝ የመቀየር ሥራው ይቀጥላል፤ 400ዎቹ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት ሲገቡ፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት የአንበሳ አውቶቡሶች ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ይሆናል፤ መጪው ጊዜ ለልጆቻችን እና ለኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪና ብሩህ ነው፤ ጋዝ እናወጣለን ብለን ጋዝ ማውጣት ችለናል፤ መናገር ብቻ ሳይሆን፤ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎችን አልፎ ስራው ተጠናቅቆ ለህዝብ ጥቅም ማዋል የአንድ መንግሥት መለኪያ ነው፤ የምንናገረውን ወደ ተግባር መቀየር የኢትዮጵያ መንግሥት መታወቂያ ነው፤ በአፍሪካም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚናገረውን ይፈጽማል የሚል እሳቤ እየጎላ መጥቷል፤ የትራንስፖርት ወጪ ከቀነስን፤ አሁን በተጀመረው የቤት ፕሮግራም በተቻለ መጠን ቤት ማቅረብ ከቻልን፤ ምግብ ላይ የጀመርነውን ስራ ከሰራን ለውጥ እናመጣለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ፣ ትራንፖርት እና ቤት ሰውን እያሰቃየ መሆኑን ጠቁመው፤ እነዚህ ሦስት ጉዳዮች እየተፈቱ ሲሄዱ ሰዎች ባላቸው ገቢ ልክ የተሻለ ኑሮ የሚያስችል እድል እንደሚያገኙ አመልክተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ተስፋ በብዙ መንገድ እየታየ ነው፤ በልማቷ በጣም አመርቂ ውጤቶች እየታዩ ነው፤ ከጥረት፣ ከስራ እና ከትጋት ውጪ የሚገኝ ውጤት የለም፤ በልፋት ብቻ ነው ሀገር የምንቀይረው፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን የነዳጅ ተጠቃሚ አውቶቡሶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ጋዝ እንቀይራለን፤ በቀጣዮቹ ዓመታትም የጋዝ አውቶቡሶችን ቁጥር በየደረጃው በማሳደግ፣ በአዲስ አበባ በነዳጅ የሚሠሩ የከተማ አውቶቡሶችን በሙሉ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር ታቅዷል፤ #ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ 16 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint