በክረምት እርሻ አፈጻጸም መልካም ውጤት ተመዝግቧል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በክረምት እርሻ አፈጻጸም መልካም ውጤት ተመዝግቧል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በባሌ ዞን የክረምት እርሻ አፈጻጸምን መመልከታቸውን ገልጸው መልካም የሚባል ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።
በዘንድሮው ክረምት ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሥጋት የነበረ ቢሆንም በመንግሥትና በሕዝብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መልካም የሚባል አፈጻጸም ሊመዘገብ መቻሉን ገልጸዋል።
አክለውም ኢኮኖሚያችን አይበገሬ ሆኖ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን በጽናት እንዲቋቋም፤ ቀድሞ መዘጋጀትና አማራጮችን ማስፋት የግድ መሆኑን አስገንዝበዋል።