Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ጋር ያደረጉት ውይይት ለኮፕ32 ልምድ የተቀሰመበት ነው – ቢልለኔ ሥዩም

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ያደረጉት ውይይት ለኮፕ32 ልምድ የተቀሰመበት ነው አሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም፡፡

ኃላፊዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቱርክዬ አንታሊያ በተካሄደው የኮፕ31 የመሪዎች ጉባኤ ላይ ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ባደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን ግንኙነት በተመለከተ መምከራቸውን አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ባደረጉት ውይይት የሀገራቱ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተከናወኑ ተግባራትን መገምገማቸውን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ በኢኮኖሚና በተለያዩ መስኮች ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው አውስተው፤ ባለፉት ዓመታት ትብብራቸውን ለማጠናከር የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

የቱርክዬ ፕሬዚዳንት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማሳደግ የሚያስችሉ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በአንታሊያ ያደረጉት ውይይት ከዚህ ቀደም የተደረሱ መግባባቶች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ለመፈተሽ ጥሩ አጋጣሚ መፍጠሩን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የ32ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ32) አስተናጋጅ ሀገር በመሆኗ፤ ከአንታሊያ ምን መማር እንችላለን በሚለው ጉዳይ ልምድ የተቀሰመበት ውይይት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #fanamediacorporation

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.