የኦቢኤን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ገቢሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ገቢሳ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ ግዛቸው በኦሮሚያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ውስጥ ከሪፖርተር እስከ ዋና አዘጋጅነት፣ በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት እና የሕዝብ አስተያየት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።
አቶ ግዛቸው ገቢሳ ከሚያዚያ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፤ በሚዲያ ኢንዱስትሪውን በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
አቶ ግዛቸው ባለትዳር እና የአንድ ወንድና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ።