Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም የኢትዮጵያን የኮፕ32 ዝግጅት ይደግፋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ለኮፕ32 የምታደርገውን ዝግጅት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው አሉ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በቱርክዬ አንታልያ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ31 ጎን ለጎን ከዋና ዳይሬክተሯ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የተቋሙ የበካይ ጋዝ ልቀት ክፍተትና ለአየር ንብረት ለውጥ የመጣጣም ክፍተት ሪፖርቶች የኮፕ32 ዝግጅቶችን በሚደግፉበት ሁኔታ እንዲሁም ክፍተቱን ለመቀነስ የሚያስፈልጉ ሀብቶችን በተመለከተ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
በተጨማሪም በአፍሪካ ታዳሽ ኃይልን ስለማስፋፋትና ከፍተኛ ሙቀትን ጨምሮ ከከባድ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ተጽዕኖ አንጻር የከተሞችን ተቋቋሚነት ስለማጠናከር መክረዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያን የኮፕ32 ዝግጅትና የአዲስ አበባው ጉባኤ የሚያስቀምጣቸውን ቅድሚያ ጉዳዮች በሚወስንበት ሂደት ተቋማቸው ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.