Fana: At a Speed of Life!

ሰሞኑን በጋሞ ዞን እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ናዳ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ሰሞኑን በጋሞ ዞን እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ናዳ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በናዳው የሰው ህይወት ከማለፉ ባሻገር አንድ ሰው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል፡፡

የጋሞ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ማርቆስ እንዳሉት÷ በናዳው 21 አባወራ እና 176 የቤተሰብ አባላትም ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
በተመሳሳይ በዞኑ ቁጫ ወረዳ 2 ቤት ላይ የመስመጥ አደጋ በመድረሱ 5 አባወራ እና 25 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ነው የተባለው፡፡
የዝናቡ ሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑም በተራራማ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቶ ተስፋዬ መርቆስ ማሳሰባቸውን ከጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.