Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው – ማህሙድ አሊ ዩሱፍ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህመድ አሊ ዩሱፍ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው አሉ።

ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ ለተካሄደው የተሳካ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

የምርጫው ሂደት ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት እንዲሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየውን ሙያዊ ብቃት እና ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።

ሊቀመንበሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በታማኝነት፣ ሰላማዊ እና ግልጽነት ባለው የምርጫ ሂደቶችን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን መግለጻቸውን የህብረቱ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.