Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓል በመላው አገሪቱ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ አገሪቱ ተከበረ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የደመራ በዓል ትናንት በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ የዋለ ሲሆን ዛሬም በእምነቱ ተከታዮች የመስቀል በዓል ተከበረ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከዚህ ቀደም በመሰባሰብ የሚከበረው የመስቀል በዓል በኮሮና ቫይረስ መከሰት ሳቢያ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲከበር ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ “በደመራ በዓል ባደረጉት ንግግር መስቀልን ባየን ቁጥር እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የምናስታውስበትና አዳኝነቱን፣ ፍቅሩን፣ ሰላሙንና አንድነትን የምናገኝበት መሆኑን መገንዘብ ይገባል” ብለዋል፡፡

“እኛም የመስቀልን ትረጉም ካወቅን ሰላምን፣ አንድነትን እንገኛለን፤ ወደ ሰላም ወደ ልማት እንጂ ወደ ጥፋት አንዳናተኩር ያደርገናል” ብለዋል አቡነ ማትያስ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.