299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው በትናንትናው እለት ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ያለ ህጋዊ ሰነድ የገቡና በጅዳ ከተማ በእስር ላይ የነበሩ ናቸው ነው የተባለው።
ከሳዑዲ መንግስት ጋር በመተባበር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት ኢትዮጵያውያን ውስጥ 264ቱ ሴቶች ሲሆኑ 35ቱ ደግሞ ህጻናት መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።