Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቅን አስመልክተው ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 23 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ የተከበረውን የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቅን አስመልክተው ምስጋና አቅርበዋል።
 
ርእሰ መስተዳድሩ በምስጋና መልዕክታቸውም “ከጥንት የገዳ ስርዓት የወረስነው እርስ በርስ የመደማመጥ፣ የመከባበር፣ ለሰላማችንና ለነጻነት አብረን መቆም ባህልን ነው” ብለዋል።
 
“በመሆኑም ይህ ከገዳ ስርዓት የወረስነው ባህል ተጠናክሮ መቀጠሉን ዛሬ በተከበረው የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ላይ አረጋግጠናልም” ነው ያሉት።
 
በዚህም የዛሬው በዓል ያለአንዳች የጸጥታ ችግር በሰላም መከበሩና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ አባገዳዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በመከበሩ እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን ብለዋል።
በዓሉም በሰላምና በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ያስቻሉትአባገዳዎች፣ የጸጥታ አስከባሪዎች፣ የከተማዋ ቄሮና ቀሬ ፣ የመዲናይቱ ነዋሪዎች፣ የበዓሉ ተሳታፊዎች እና የሚዲያ ተቋማትን አመስግነዋል።
አቶ ሽመልስ አያይዘውም የዛሬው በዓል በድምቀትና በሰላም እንደተጠናቀቀ ነገም በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረውም ኢሬቻ በሆራ አርሰዴ በሰላም እንደሚጠናቀቅም እምነታቸው የጸና መሆኑን ገልፀዋል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.