የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሄደ
ፕሬዚዳንቷ በመክፈቻ ንግግራቸው፦
- ያለፈው አመት ስኬታማ እንደነበር አንስተዋል፣
- ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት ዳግም በማደስ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸው፣
- በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በተሰሩ ስራዎችና የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት፣
- ሲንከባለሉ የቆዩ ፕሮጄክቶችን በስኬት ማጠናቀቅ የተቻለበትና ትልቅ ተሞክሮ እንደተገኘበት ጠቅሰዋል
- በተጨማሪም ካለፉት አመታት በተሻለ የወጪ ንግድ ገቢ የተገኘበት መሆኑ፣
- 5 ቢሊየን ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማሳካት የተቻለበት፣
- ለሶስት ሚሊየን ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩ፣
- የሃገሪቱ የ10 አመት የሃገሪቱ ፍኖተ ብልፅግና የተዘጋጀበት፣
- በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር መድረክ በመፍጠር ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱ ፣
- ኮሮናን በመከላከል ረገድ አፋጣኝ የመከላከል አቅም የተገነባበት መሆኑ፣
- በኮሮና ምክንያት የሚፈጠረውን የምግብ እጥረት ለመቋቋም ምንም መሬት ጦሙን እንዳያድር ማድረግ የተቻለበት፣
- አመቱ በጥቅሉ በርካታ ታሪካዊ ስኬቶችን የተስተናገደበት ነበር፣
- ከስኬቶቹ ባሻገር በርካታ ተግዳሮቶች የታዩበት ነበር፣
- ከዚህ ውስጥ በኮቪድ19 ምክንያት ሃገራዊ ምርጫ መራዘም፣
- በተፈጠሩ ግጭቶች የዜጎች ህይዎት የጠፋበትና ብሎም የተፈናቀሉበት፣
- ያልተገቡ የህግ ጥሰቶች የተፈጸሙበት፣
- የበረሃ አንበጣ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰበትና በርካታ አጋጣሚዎች የተከሰተበት እንደነበር ጠቅሰዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።