Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በተያዘው ዓመት ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 789 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ በ3 ወራት ብቻ ከ 500 ሚሊየን ብር በላይ ሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ከዳር ለማድረስ የገቢ ማሰባሰብ ስራው በሰፊ ንቅናቄ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

የከተማዋ የታላቁ የኢትዮጵያ ህደሴ ግደብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ÷ በበጀት አመቱ ከ789 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማሰባሰብ አቅዶ ባለፉት 3 ወራት ብቻ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት አስታውቋል።

የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ በእነዚህ ወራት የተሰበሰበው ገቢ በአመቱ ከታቀደው በላይ ገቢ ሊሰበሰብ አንደሚችል አመላካች ነው ብለዋል።

ለዚህም ምክንያቱ የሁሉም ኢትዮጵያያን አሻራ ያረፈበት ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሀ ሙሌት መጠናቀቅ እና ለገቢ ማሰባሰቢያ በሀገሪቱ ሁሉም ቦታዎች የሚዞረው ዋንጫ ነው ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የህዳሴው ዋንጫን በአስሩም ክፍለከተሞች በማዘዋወር ገቢ እየሰበሰበ ይገኛል።

ይህም ህብረተሰቡ ለግድቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር እንዳገዘውም የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ ተናግረዋል።

የህዳሴው ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ እስከባለፈው አመት መጨረሻ ከ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አቶ ምስክር ነጋሽ አክለው ገልጸዋል።

በዙፋን ካሳሁን

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.