Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአፍሪካ የደህንነት ጥናት ተቋም ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአፍሪካ የደህንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ዶክተር ፎንቴህ አኩም እና የተቋሙ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተርና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ከሆኑት ዶክተር ሮባ ሻራሞ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በዚህ ወቅት አፍሪካዊያን በተለያዩ መስኮች ላይ በትብብር መስራትን አጠናክረው መቀጠል እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር ተቋሙ ሰፊ እንቀስቃሴ እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።

ከዚያም ባለፈ ተቋሙ የጋራ አጀንዳዎቻችንና ሊያግባቡን የሚችሉ የፖሊሲና ስታራቴጂ ጥናቶችን ማከናወን ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበትም ነው ያሉት።

የደህንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ዶክተር ፎንቴህ አኩም በበኩላቸው ÷ድርጅቱ በተለያዩ አፍሪካ አገራት ላይ በሰላምና ፀጥታ ላይ በርካታ ጥናቶችንና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያም በውጭ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ማሰልጠኛ ተቋም እና ከብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ጋር ተያይዞ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በቀጣይም በአፍሪካ የጋራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲኖር ከማድረግ አንጻር ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ዶክተር ፎንቴህ አኩም መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.