Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጎርጎራን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር አንዱ አካል የሆነውን የጎርጎራ ፕሮጀክት መተግበሪያ አካባቢን ጎብኝተዋል።

በሀገር ደረጃ 3 መዳረሻዎችን በ3 ቢሊየን ብር ለማልማት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሮች እየተከናወኑ ነው።

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች አንዱ በጣና ሐይቅ ዳርቻ የሚገኘው የጎርጎራ ፕሮጀክት ነው።

በጎርጎራ ፕሮጀክት የቱሪስት ፍሰትን ለመሳብና የአካባቢ ጸጋን በመጠቀም የተለያዩ ልማቶችን ለመተግበር ታቅዷል።

ዘመናዊ ካፌና ሬስቶራንት፣ የብስክሌትና ፈረስ መጋለቢያ፣ ባህላዊ መንደሮች ልማት፣ የግብርና ምርምር፣ የዓሳ ማስገሪያ መዳረሻን ማልማትና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.