ጠ/ሚ ዐቢይ ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር ክብረወሰን ማሻሻሏን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር ክብረወሰን ማሻሻሏን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት በመሆንሽ አኩርተሽናል ብለዋል፡፡
እንዲሁም በተግባር የታየ ልዕልና ይኼ ነው! ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
ለተሰንበት ግደይ ሌሊት በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ክብረወሰን በማሻሻል ማሸነፏ የሚታወስ ነው፡