Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ ጋር ተወያዩ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ የተወያዩት ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር በመሆን ነው፡፡
 
ተወካዩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ የልዑካን ቡድናቸው ይዘው መምጣታቸው ተነግሯል፡፡
 
ዛሬ ጠዋት በተካሄደው በዚህ ውይይት በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮሩን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.