Fana: At a Speed of Life!

በአርብቶ አደር እና በመንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በአርብቶ አደር እና በመንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

ስልጠናው ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለልዩ ድጋፍ ቦርድ አባላትና ለተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ እንገሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ልዩ ድጋፍ ዳይሬክተር ጀነራል ፕሮፌሰር ደገፋ ቶሎሳ ÷ በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ተመጣጣኝ ልማት ማረጋገጥና በክልሎችና በአጎራባች  ክልሎች መካከል ግንኙነቶች እንዲዳብሩ ማድረግ የሰላም ሚኒስቴር ከተሰጠው ሀገራዊ ተልዕኮ አንዱ ነው ብለዋል።

ይህን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣትም  የአርብቶ አደር ፖሊሲ እና የመንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ ሲያረቅና ሲያስገመግም ቆይቶ ፖሊሲዎች ፀድቀው  ወደ ተግባር መገባቱን አመላክተዋል፡፡

አያይዘውም የአርብቶ አደር ፖሊሲ የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ማሻሻልና ማዘመን እንዲቻል በጥንቃቄ የተዘጋጀ ፖሊሲ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የመንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ የክልል መንግስታትን ከፌደራል መንግስት እንዲሁም ክልልን ከክልል ጋር በማስተሳሰር ጤናማ ግንኙነቶች እንዲኖር ያስችላል ተብሏል፡፡

የስልጠናው ዓላማ የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ አመራርና ባለሙያዎች ስለ ፀደቁት ፖሊሲዎች ጥልቅ እውቀት ኖሯቸው በስራቸው ላሉ ባለሙያዎች ግንዛቤ በመፍጠር  ለፖሊሲዎች  ዓላማ መሳካት ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆኦ እንዲያበረክት ያለመ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.