በቁም እንስሳት ግብይት የሞባይል መተግበሪያ ቴክኖሎጅ ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሰባቱ ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳድሮች በቁም እንስሳት ግብይት የሞባይል መተግበሪያ ቴክኖሎጅ ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡
በውይይቱ የአማራ፣ የአሮሚያ፣ የአፋር፣ የሶማሌ፣ የትግራይ ክልሎች እንዲሁም የአዲስአበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የንግድና የገቢ ልማት ቢሮ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የቁም እንስሳት ግብይት ሞባይል መተግበሪያ ቴክኖሎጅ በክልሎቹ እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የግብይት ስርዓቱ የሚካሄድባቸው 47 የግብይት ቦታዎች መመረጣቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ያለውን የቁም እንስሳት ሀብት በክልላዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ገበያ ስርአት ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የአማራ ክልል የንግድና ግብይት ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢታ ገበያው ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የቁም እንስሳት ጥቅም ላይ ለማዋል ዘመናዊ የግብይት ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!