ከዛሬ ጀምሮ ለምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት እንደሚጀመር ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረገውን የቁሳቁስ ዝግጅት ከዛሬ ጀምሮ ወደ የምርጫ ጣቢያዎች ስርጭት እንደሚጀምር ገለጸ፡፡
ቦርዱ አጠቃላይ የምርጫ ዝግጅት እና ቀሪ ስራዎችን በሚመለከት ለፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ሪፓርት እያቀረበ ይገኛል፡፡
እስካሁን ባለው ዝግጅትም የምርጫ ኦፕሬሽን፣ የሲቪክና የመራጮች ትምህርት፣ ስልጠና፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ፣ የውጭ ግንኙነት (ስርዓተ ፆታ) አካታችነት ላይ በተሰሩ ስራዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
673 የምርጫ ክልል የተዘጋጀ ሲሆን 49 ሺህ 407 የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ተመርጧል።
የዞንና የምርጫ ክልል ቢሮ እየተከፈተ ይገኛል፤ የሰነድና የቁስቁስ ዝግጅት ተጠናቆ ከዛሬ ጀምሮ በሶስት ክፍል እንደሚሰራጭ ነው የተገለጸው።
የተለያዩ ስልጠናዎች የተጀመሩ ሲሆን የመሪና የዋና አሰልጣኞች ስልጠና በአብዛኛው መጠናቀቁም ተጠቅሷል።
የስነ ዜጋና መራጮች ትምህርት ለመስጠትም 115 የሲቪክ ማህበራት ተመልምለው ለ64ቱ ዕውቅና ተሰጥቷል።
የተለያዩ መረጃዎችን ለመራጮች ለማድረስ የተለያዩ መገናኛ መንገዶችን በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ እንደሚለቀቅ ይጠበቃል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የመወዳደሪያ ምልክቶች ባለፈው ሳምንት ይፋ መደረጋቸው የሚታወስ ነው።
ቦርዱ አሁን ተጨማሪ የሰራቸው ስራዎችና ቀሪዎቹ ላይ ማብራሪያ እየሰጠ ሲሆን ከፓርቲዎቹ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በቦርዱ አመራሮች ምላሽ እየተሰጠበት ይገኛል።
በኃይለኢየሱስ ስዩም
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!