የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት የጠንካራ ግንኙነት ማሳያ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ጠንካራ ግንኙነት ማሳያ ነው አለ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራማኒያም ጃይሻንካር ጋር ተወያይተዋል።
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የህንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው÷ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ለሀገራቱ ግንኙነት መጠናከር ማረጋገጫ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡