በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ በጅማ የልማት ስራዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰመስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች ልዑክ በጅማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ለስራ ጉብኝት ጅማ ገብተዋል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር የውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የጅማ ዞን እና የጅማ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ልዑኩ በጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ የሻሸመኔ የችግኝ ጣቢያን ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ ላይ አቶ ሽመልስ በጅማ ዞን በአንድ ዓመት ውስጥ በስንዴ ምርት ላይ የታየው ምርታማነት አገሪቱ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለማምረት ያቀደችው የስንዴ ምርት መጠን እንደሚሳካ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!