Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ …

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራሁ ነው አለ።

የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በማዕከሉ አምስት የክልልና አራት የፌዴራል ተቋማት 35 የተለያዩ አገልግሎቶች እየሰጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

በዚህም ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ 12 ሺህ 552 ዜጎች አገልግሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዚህ በፊት በአገልግሎት ላይ ከሕብረተሰቡ ሲነሳ የነበረውን ቅሬታ እየፈታ እንደሚገኝ ገልጸው÷ በዚህም ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበትና ሀብት መቆጠብ እንዳስቻለ አብራርተዋል።

በክልሉ የማዕከሉን ተደራሽነት ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ የአምስት ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።

በቦንጋ፣ ታርጫ፣ ቴፒ እና አመያ ከተሞች እንዲሁም ሚዛን አማን ላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የማዕከሉ ግንባታ ስራ በሌሎች 15 ከተሞችም እንደሚቀጥል አቶ የሺዋስ ጠቁመዋል።

በአድማሱ አራጋው

👉ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች የፋና ዲጂታል አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.