Fana: At a Speed of Life!

ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍና ለሆስፒታሎች ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር እርምጃውን ተከትሎ ለተፈናቀሉ  ዜጎች ድጋፍ አድርጓል።

በመቀሌ፣ አብዱራፊ፣ አዲግራት እና ሽሬ ለሚገኙ 9 ሺህ 125 አባወራዎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉን ነው የገለፀው።

በዚህም የፕላስቲክ መጠለያ ፣ ብርድ ልብስ ፣የመኝታ ምንጣፎች እና ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች ከተፈናቃይ ዜጎች መቅረቡ ኮሚቴው ገልጿ።

በተጨማሪም በሰሜን ትግራይ በአዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና ሽሬ ለሚገኙ ስምንት ሆስፒታሎች ምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ማከፋፈሉን ነው ያስታወቀው።

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀ ሲሆን በሌሎች አካላት የሚደረገው ድጋፍ ከፍ እንዲል ጠይቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.