በኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተመራ ልዑክ ጅቡቲ ገባ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡
የልዑካን ቡድኑ ጅቡቲ ሲደርስ የጅቡቲ ፖሊስ ኃይል ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱላሂ አብ ፋራህ ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ፣ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል ፡፡
የልዑካን ቡድኑ በሚኖረው ቆይታ በስልጠናና በጠረፍ ደህንነት ዙሪያ ከጅቡቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጁቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!