የህዳሴ ግድብ ግንባታ በፍጥነት መጠናቀቅ ለሶስትዮሽ ድርድሩ መሳካት ወሳኝ ነው – ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በፍጥነት መጠናቀቅ ለሶስትዮሽ ድርድሩ መሳካት ወሳኝ በመሆኑ የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፕሮፌሰር ያዕቆም አርሳኖ ተናገሩ።
ፕሮፌሰሩ ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ተማሪዎች ስለ ግድቡ አስተዋጽኦና እየተደረገ ስላለው ድርድር ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በሶስትዮሽ ድርድሩ በኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች በማከል አንዱ የሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ምሁር ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በወቅቱ እንደገለጹት ÷የሶስትዮሽ ድርድሩ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ መልኩ ነው፡፡
ግድቡ ለአገሪቱ ወሳኝ ፕሮጀክት መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ያዕቆብ÷ የግንባታው በፍጥነት መጠናቀቅ ለድርድሩ ወሳኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ድጋፉን ማጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡
ግድቡ ለአገሪቱ እድገት ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ለማከናወን ተጨማሪ አቅምና ጉልበት በመጠቀም ግንባታው እንዲፈጸም ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጸደቀ ላምቦሬ በበኩላቸው÷ የፕሮፌሰር ያዕቆብ ማብራሪያ ጥናትና ምርምር ለማድረግ መነቃቃት ፈጥሯል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!