Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ጀማል በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሮ ኤዥያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን የኢትዮጵያ የቆንስላ ጽህፈት ቤት መሪ አምባሳደር ጀማል በከር አዲስ ከተሾሙት በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሮ ኤዥያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አምባሳደር ፋጥማ አብደላ አልዴን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በበየነ-መረብ በተካሄደው ውይይት በኢትዮጵያና በባህሬን መካከል ያለው ሁለትዮሽ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖኖሚ፣ የማህበራዊና ባህላዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ግንኙነቶች በሚጠናከርበት ዙሪያ መክረዋል ፡፡
በተጨማሪም አምባሳደር ጀማል ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በመጪው ብሔራዊ ምርጫ እንዲሁም የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አምባሳዳር ፋጥማ አብደላ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለትዮሽና ቀጠናዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ጠቅሰው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ አካባቢያዊና አለም አቃፍ ግንኝነቶች ይበልጥ ለማጠናከር በቅርበት ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ፤ መልሶ መቋቋምና የሰበዓዊ ድጋፍ ዙሪያ እየተደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ግንዛቤ መያዛቸውን፤ ከህዳሴ ግድብ ጋር ያሉ ልዮነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ-የሱዳን ድንበር አለመግባባቶች በድርድርና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያለቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በሁለቱም አገራት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር እንዲጎለብት የባህል ትስስር እንዲጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት በመፈራረም ህጋዊ የሰው ዝውውር እንዲኖር በጋራ ለመስረት መግባበት ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.