Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት አድርጊያለሁ – የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል፡፡
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ በቅድመ ምርጫ፣በምርጫ ዕለትና ድህረ ምርጫ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
የምርጫ ቁሳቁሶች ድሬዳዋ ከትላንት ጀምሮ መግባታቸውን ተከትሎ በተለይ ዛሬ ደግሞ ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ ሲሰራጩ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ፖሊስ በምርጫው ቀንም ይሁን በድህረ ምርጫ ቀናት በተመሳሳይ የህዝቡን ደህንነት መጠበቅና ችግር እንዳይፈጠር ከነዋሪው ጋር ለመስራት የአማካሪ ምክር ቤት መቋቋሙንም እንዲሁ አንስተዋል::
6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህዝቡ ከፖሊስ ጋር እንዲሰራም ጠይቀዋል ኮሚሽነር አለሙ መግራ፡፡
በሳራ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.