ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በጉራጌ ዞን ዝግጅት ተጠናቋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰኔ 14 2013ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የጉራጌ ዞን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
ለምርጫው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በዞኑ ደርሰው ወደ የምርጫ ክልል እየተላኩ ነው፡፡
እስከ ነገ እኩለ ቀን ሁሉም የምርጫ ቁሳቁሶች በየምርጫ ክልሉ ተጉዘው እንደሚጠናቀቁ የጉራጌ ዞን እና የየም ልዩ ወረዳ የምርጫ ቦርድ አስተባባሪ አቶ አሳልፈው መኩሪያ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ፡፡
የየም ልዩ ወረዳን ጨምሮ በ13 ምርጫ ክልል፣በ923 ምርጫ ጣብያ ከ630ሺህ በላይ መራጮች ድምፃቸውን ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
በታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!