በአሸባሪው የህወሓት ተጠርጣሪ አባላት ላይ በዚህ ሳምንት ክስ ይመሰረታል
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት 42 ተጠርጣሪ አባላት ላይ በዚህ ሳምንት ክስ እንደሚመሰረት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፈቃዱ ጸጋዬ አስታወቁ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በሕግ አግባብና በፍትሕ መንገድ ላይ ሳይሆን በሌሎች ግፊቶች ነጻ ለመውጣት ሲጣጣሩ እንደነበሩ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ፥ 42ቱ ተጠርጣሪ የአሸባሪው ህወሓት አባላት በቀዳሚ ምርመራና በዋና ምርመራቸው ወቅት ጉዳያቸውን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡
በተለይም ያልሆኑ ሰበባ ሰበቦችን በመቃረም የፍርድ ሂደቱ ዘገየ ለማስባል መሞከራቸውን ያመለከቱት አቶ ፈቃዱ፥ በሕግ አግባብና በፍትህ መንገድ ሳይሆን በሌሎች ግፊቶች ነጻ እንወጣለን በሚል ሒሳቦችን ሰርተው ከእስር ለመውጣትም ሲጣጣሩ ቆይተዋል ብለዋል ፡፡
ነገር ግን ምርመራው ከታሰበው በላይ በፍጥነት በመጠናቀቁ ይህ ስሌታቸው እንዳልሰራ ማመላከታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በሰሩት ልክ ሕግ ተገቢውን ፍርድ ይሰጣቸዋል ያሉት አቶ ፈቃዱ፥ በቀጣዩ ሳምንት ተጠርጣሪዎቹ ለክስ እንደሚቀርቡ አመላክተዋል ፡፡
ክሱ የወንጀል ክስ በመሆኑም ፍጥነቱ ምን ያህል ተቀናጅቶ እንደተሰራበት የሚያመላክትም ነው ብለዋል ፡፡
በብዛት በምርመራና በሰበባ ሰበብ እንዲሁም በምስክር ማሰማት ሂደት ችግሮች ባያጋጥሙ ኖሮ ከዚህ ባነሰ ጊዜም ክሱ ይመሰረት እንደነበር አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!