Fana: At a Speed of Life!

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የወራቤ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አደጋ መከላከል ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ቢላል አወል እንደገለጹት÷ከረፋዱ 5 ሰዓት ገደማ ካሊድ ወንዝ ላይ ኤፍኤስ አር ሲኖ ትራክ እና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተጋጭተው ነው አደጋው የደረሰው።
በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአደጋው ተጎጂዎች በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን÷ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም አስተባባሪው ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.