Fana: At a Speed of Life!

በመንግስት የሚሰጡ መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የትግራንይ ህዝብ ሳይሆን ወንጀለኛውን ህወሓትን ብቻ ነው- ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል እና የክልል መንግስታት የሚሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ውቅር አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ ወንጀለኛውን ህወሃትን ብቻ መሆኑን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ ÷ የህወት ፕሮፓጋንዳ አራማጆች እና አጋሮቻቸው የፌደራል እና የክልል አመራሮች የሚናገሩትን በመጠምዘዝ ለብዙ ወራት ሲሸርቡ ከቆዩት የሐሰት ዜናዎች እና አጀንዳዎቻቸው ጋር ለማጣጣም መሞከራቸውን እንደቀጠሉ አብራርቷል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሃት አሸባሪ ድርጅት እንደ ሆነ ማወጁን በማገናዘብ፣ የፌደራል እና የክልል መንግስት የሚሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ውቅር አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ ወንጀለኛውን ህወትን ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.