Fana: At a Speed of Life!

የጡት ማጥባት ሳምንት ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ይከበራል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጡት ማጥባት ሳምንት ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ የግንዛቤ መስጫ ፕሮግራሞች እንደሚከበር ተገለጸ።

በጤና ሚኒስቴር የስርዓት ምግብ ባለሙያ ዶክተር በላይነሽ ይፍሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ሳምንቱ በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ ፕሮግራሞች ይከበራል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ተቋማት የህጻናት ማቆያ በማዘጋጅት እናቶች ህጻናት ልጆቻቸውን ጡት እንዲያጠቡ ቢመቻችም በኮቪድ19 ምክንያት መቋረጡን ጠቅሰዋል፡፡

ጡት ማጥባት ጥሩ የህይወት ጅማሮን ከማቀናጀቱ ባሻገር ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ ለተሞላ ጤና እና ለተስተካከለ ቁመና እና ለስርዓተ ምግብ ዋስትና ጥቅሙ ከፍ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለሰው ልጆች የተሰጠ ተፈጥሯዊ መብት በመሆኑ ሊደገፍ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

እናቶችም ህጻናትን እስከ ስድስት ወር ድረስ ጡት ማጥባት እንዳለባቸውና እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ከተጨማሪ ምግብ ጋር ማጥባት እንደሚገባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ይህም መቀንጨርን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከልና ለህጻናቱ ጤናማ እድገት ወሳኝ መሆኑንም ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.