Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴር ከኬር ኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር ኬር ኢትዮጵያ ከተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በግብርናው ዘርፍ የስርዓተ ፆታን አቅም ለማጎልበት የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዓይናለም ንጉሴ ስርዓተ ፆታ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራታችን በግብርናው ዘርፍ ለምናከናውነው ሁለንተናዊ ስራ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች በመሆናቸው ከዚህም አብዛኛዎቹ በገጠሩ ክፍል የሚኖሩ ሲሆን ሴቶች የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው እና የሴቶችን የኑሮ ደረጃ በመቀየር ሃገራዊ ብልፅግና ለማፋጠን ብሎም በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ሴቶች የላቀ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ፕሮጀክቱ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡
የኬር ኢትዮጵያ ተወካይ ዳይሬክተር ሳሙኤል እሸቱ ድርጅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ላይ አጠቃላይ የማህበረሰብ ፍትህ፣ የልማት ስራዎችን እና ህይዎትን የማዳን ስራ ላይ በዋናነት እንደሚሰራ ጠቅሰው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
የዊጎ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አይኔ ሀብታሙ የዚህ ፕሮጀክት መንቀሳቀሻ በጀት የተገኘው ከቢል ኤንድ ሜሌንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ይህንን ስራ ለመስራትም ፕሮጀክቱ ለአምስት ዓመት የሚቆይ እና ለመነሻ ያህል 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በጀት የተመደበለት መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ መግለጻቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.