የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ የድሬደዋ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ የድሬደዋ ወጣቶች ሽኝት መደረጉ ተገለፀ፡፡
የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ሀገር የማፍረስ ተልኮና ተግባር ለመከላከልና ለማምከን ለሀገሬ ዘምታለሁ ብለው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ለወሰኑ የድሬደዋ ወጣቶች ነው ሽኝት የተደረገው፡፡
በሽኝት መርሃ ግብሩ የድሬደዋ ከተማ የአስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጅሀርና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከድሬደዋ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!