Fana: At a Speed of Life!

የቤንች ሸኮ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል የቤንች ሸኮ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
የዞኑ ሴቶች ህጻናት ወጣቶች መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ባንቺ አየሁ ዳዲ እንደገለጹት፥ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ከ8 ሚሊየን በላይ ብር ድጋፍ ተደርጓል።
ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በሴቶች አደረጃጀት ብቻ ከ1ነጥብ 2 ማሊየን ብር በላይ የአይነትና የጥሬ ገንዘብ በማሰባሰብ ለክልሉ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ገቢ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ክልል ሀብት አሰባሳቢ ኮሜቴ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ አስቴር ከፍታው ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት፥ አሸባሪው ቡድን ጋር እየተደረገ ያለውን ትግል በስኬት ለማጠናቀቅ በክልሉ ከተለያዩ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገ ነው ።
በክልሉ በመጀመሪያ ዙር በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ከ37 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ ለመከላከያ ሚኒስቴር ማስረከብ እንተደቻለ ተናግረዋል።
እንደወይዘሮ አስቴር ገለጻ፥ በክልሉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 250 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱን መግለጻቸውን ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.