ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉዲፈቻ የሚያሳድጓትን ሕፃን ተረከቡ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉዲፈቻ የሚያሳድጓትን አንዲት ሕፃን ልጅ በዛሬው ዕለት ተረክበዋል።
በጉዲፈቻ ለተረከቧት ሕፃን ዲቦራ የሚል መጠሪያ ስም ያወጡላት ሲሆን÷ ከልጆቻቸው እኩል ሊያሳድጓትም ቃል ገብተዋል።
ከወይዘሮ አዳነች በተጨማሪ የጉለሌ እና የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ ሌሎችም በግላቸው አንድ አንድ ሕፃናትን ለማሳደግ ተረክበዋል።
ሕፃናቱን ለጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው የማስረከቡ ስነ-ስርዓት የክፍለ ከተማ አመራሮች እና የከተማዋ ባለሃብቶች በተገኙበት ተካሂዷል።
በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር እንደ አንድ አጀንዳ ተይዞ እየተሰራበት ባለው “አንድ ቤተሰብ ለአንድ ሕፃን” መርሃ ግብር እስካሁን 306 ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት አዲስ ቤተሰብ ማግኘት ችለዋል መባሉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!