የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት ስንቅ አዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የዋና መስሪያ ቤት እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊቱ ስንቅ አዘጋጅተዋል ፡፡
በስንቅ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በቀጣይነት ግንባር ድረስ በመሄድ ለመከላከያ ሰራዊቱ ስንቅ የማቀበል ድጋፉ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!