ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊላክ የነበር 2 ሺህ 900 ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ የሲሚንቶ ማጓጓዣ ከባድ ተሽከርካሪ በድብቅ ተጭኖ ከደብረ ብርሃን በአዲስ አበባ በኩል ወደ ሰሜን ሸዋ ሊጓጓዝ የነበረ 2ሺህ 900 ጥይት ተያዘ፡፡
ጥይቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ሳይወጣ በተደረገበት ልዩ ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋሉን የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል፡፡
ጥይቱ የክላሽንኮቭ መሳሪያ መሆኑን የጠቀሰው ግብረ ሃይሉ÷ ለሸኔ የሽብር ቡድን እንዲደርስ ታስቦ ሲጓጓዝ መያዙን ጠቁሟል፡፡።
ተጠርጣሪዎቹ ሲሚንቶ ከጫነ ከባድ ተሸከርካሪ በተለምዶ ደርብራተር ተብሎ ከሚጠራው የውስጥ አካል ውስጥ ጥይቶችን ደብቀው በመጫን ለማሳለፍ ሲሞክሩ አዲስ አበባ ሲደርሱ በደህንነትና በጸጥታ አካላትጥብቅ ክትትል ሲደርግባቸው ስለነበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸው ተመላክቷል፡፡
የወንጀል ድርጊቱ ተወናያን የነበረው ሹፌር እንደተደረስበት ሲያውቅ አደጋ በማድረስ ለጊዜው የተሰወረ ሲሆን÷ ተሽከርካሪውን በፒክ አፕ መኪና ሲከተሉት የነበሩት ሌሎች የወንጅሉ 4 ተጠርጣሪዎች ግን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ለተፈረጀው የሸኔ የሽብር ተግባር መፈጸሚያ የሚውሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጓጓዙ በደህንነትና በጸጥታ አካላት ጥብቅ ክትልልና ፍተሻ በተደጋጋሚ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!