ህወሓት እና ሸኔ በሚነዙት አሉባልታ የሚበተን ሀገር የለም-የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የሃይማኖት አባቶች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ሽብር ቡድን በሚነዛው አሉባልታ የሚበተን ሃገር የለም ሲሉ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ተናገሩ።
የኤፍራታና ግድም ወረዳ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ፣ የአጣየ እና የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የሃማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የኮማንድ ፖስቱ ተወካዮች ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መክረዋል።
የኢኖሼሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አህመዲን መሀመድ÷ የሽብር ቡድኖቹ ከሚነዙት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ራስን በመጠበቅ ክፍተቶችን መድፈን እንደሚገባ ተናግረዋል።
የህወሓትና ኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ተላላኪዎችን ለመዋጋት በተጎራባቾቹ የተጀመረው ጥምረት የቀጣይ የልማት ስራዎችን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።
የአካባቢው ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ተወካይ ኮለኔል ተከተል ልኬ በበኩላቸው÷ነዋሪዎቹ የሽብር ቡድኖቹን ለመዋጋት ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
የአካባቢው የጸጥታ ሃይሎችና የወጣቶች አደረጃጀትም በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
የልዩ ዞኑ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በይፋ ጋብቻ የፈጸሙትን ኦነግ ሸኔና ህወሓት በአንድ ልብ ሆነው እንደሚታገሉ አረጋግጠዋል።
ጁንታው በሚነዛው ፕሮፓጋንዳ የሚበተን ሀገር የለም ያሉት የሃይማኖት አባቶቹና የሃገር ሽማግሌዎቹ÷ በአመራሮች ዘንድ የሚሰጡ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አካባቢው የሽብር ቡድኖቹ ለእኩይ አላማቸው የሚፈልጉት በመሆኑ ተጎራባች ዞኖቹና ወረዳዎቹ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ተላላኪዎች ሐሰተኛ መረጃ በመንዛት ግጭት የመፍጠር ሙከራ በኅብረተሰቡ ትብብር እየከሸፈ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ገለጸ።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ በበኩላቸው÷ የአሸባሪው ህወሓት ከተላላኪ ሸኔ ጋር በማበር ሽብርና ግጭት በመፍጠር አገር ለማተራመስ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል።
ይሁን እንጂ የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ተላላኪዎች ሐሰተኛ መረጃ በመንዛት ግጭት የመፍጠር ሙከራ በኅብረተሰቡ ትብብር እየከሸፈ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የዞኑ አስተዳደር ከኅብረተሰቡና አመራሩ ከአጎራባች ዞኖች ጋር በመተባበር ከ200 በላይ የግጭት ነጋዴ የሆኑ የአሸባሪ ቡድኖቹ ተላላኪ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም አንስተዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ “ሸኔ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪ ወያኔ ነው” የሚለውን ቡድን ለመመከት የአማራ፣ አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!