Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ ፓርላማ አባላት የልዑክ ቡድን ጅግጅጋ ገባ

አዲስ አበባ፣ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሮፌሰር መሀሙድ መሀመድ የተመራ የኬንያ ፓርላማ አባላት ልዑክ ዛሬ ጅግጅጋ ከተማ ገባ።
ልዑኩ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርስ በሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ በሶማሊ ክልል ምክርቤት አፈጉባኤ መለው ኢብራሂም እንዲሁም በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ልዑኩ በሶማሊ ክልል በሚቆይባቸው ቀናት ከክልሉ አመራሮችና የምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት እንደሚደርግና የተለያዩ ጉብኝቶችም እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡
ልዑኩ በጅግጅጋ የተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው÷ የተለያዩ የልምድ ልውውጦችን እንደሚያደርጉ መናገራቸውን የሶማሊ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.