Fana: At a Speed of Life!

ከአሶሳ ዞን ማኦና ኮሞልዩ ወረዳ ለ2ኛ ዙር የመከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ዞን ማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ተውጣጥተው ለ2ኛ ዙር የመከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው፡፡
ሃገር የማዳን ዘመቻዉን በመቀላቀል ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመሰለፍ ለ2ኛ ዙር በተደረገው ሽኝት ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ የጸጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሀሚድ ፥ የሃገርን ጥሪ ተቀብላችሁ የዚህ ታሪክ ተጋሪ ለሆናችሁ ወጣቶች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ጀግና ለመሆንና ድል ለማግኘት በስልጠና ወቅት የሚሰጣችሁን ትምህርት በአግባቡና ጥሩ ስነ-ምግባር መቀበል ይገባችኋል ብለዋል።
ሀገር በማዳን ተልዕኮው ውስጥ በጀግንነትና በቆራጥነት በመሳተፍ ሃገራቸውንና ሕዝባቸውን እንደሚያኮሩም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በኢፌደሪ መከላከያ የላይዘን ጽ/ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ታዬ ቶሎሳ በበኩላቸው፥ ጀግንነት የጥንት አያት ቅድመ-አያቶቻቻን ነው የጀግና ልጅ ጀግና ነውና እናንተም ይህንን በመወሰናችሁ ጀግኖች ናችሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በጦር ውሎ እየተደመሰሰ ነው ያለውን ብትመለከቱ የባንዳው ቡድን በፍፁም የኢትዮጵያን ሰራዊት መቋቋም አይችልም ያሉት ኮሎኔል ታዬ ፥ በየግንባሩ በድል እየታጀብን ባለንበት በዚህ ወቅት የሰራዊቱ አባል ለመሆን በመወሰናችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በውጭና በውስጥ ጠላቶች የሚደረገውን ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ባለችበት ወቅት የቁርጥ ቀን ልጅ በመሆናቸውም አመስግነዋል፡፡
በሽኝቱ ላይ የተገኙ የሀይማኖት አባቶችም የሃገራቸውን ባንድራ ማስረከብ ወጣቶቹን በድል ሄደው በድል እንዲመለሱ በምርቃትና በጸሎት መሸኘታቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.