አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት የሕዝቡን ችግሮች ነቅሶ የሚፈታ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) መስከረም 24/2014 ሥራ የሚጀምረው መንግሥት ካሁን በፊት ከነበረው በላቀና ከአድርባይነት በፀዳ ሁኔታ የሕዝቡን ችግሮች ነቅሶ ሊፈታ የሚችል መሆን እንዳለበት የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
አዲስ የሚመሠረተው መንግሥት መስተካከልና መሻሻል ያለባቸው ህጐች እንዲስተካከሉ አስፈፃሚውን አካል መቆጣጠር እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
በሰሜን በኩል ያለውን ጦርነት በአጭር ጊዜ መቋጨት አለበት፤ ረጅም ጊዜ በወሰደ ቁጥር በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ፣ ኢኮኖሚው እየደቀቀ፣ ዘር ማጥፋ እየተፈፀመ በመሆኑ አሸባሪውን ቡድን ማጥፋት ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
በዲፕሎማሲው ዘርፍም ከተለያዩ ሀገራ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡ ለዚህም አቅም ያላቸው ዲፕሎማቶች መመደብ ይገባል ነው ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፡፡
በሀገር ሰላምና ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ ተፈናቃዮች ወደ ልማትና ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመከላከልና ለማስቆም ገለልተኛ እና ሚዛናዊ ከሆኑ መንግሥታት ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት ይባልም ብለዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት የሕዝቡን ችግር በማጥናት መሻሻልና መስተካከል ያለባቸው ህጎችና መመሪያዎች እንዲስተካከሉ መሥራት እንዳለባቸው የደብረ ብርሃነ ከተማ ነዋሪዎች ገመግለጻቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኩሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!