Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለማቋቋም የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ÷ የገንዘብ ድጋፉ ተቋሙ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀናሽ በማድረግ ያበረከተው መሆኑን ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን÷ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በአሸባሪው ህወሓት በደረሰው ጥፋት በርካታ ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን ተናግረዋል።

ድጋፉ ለክልሉ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት በአፋጣኝ ለመመልስ እንደሚያግዝም መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ እና ከእነዚህም ውስጥ 56 የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ መውደማቸው የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.