Fana: At a Speed of Life!

ወታደራዊ ስልጠና በቁርጠኝነት ሰልጥነን የሽብርተኛውን ሃይል ለመደምሰስ ተዘጋጅተናል – የብርሸለቆ ምልምል ሰልጣኞች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ35ኛ ዙር ሰልጣኞች የስልጠና መክፈቻ ስነስርዓት ተከናውኗል።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና ኣዛዥ ኮለኔል ጌታቸው አሊ ናቸው።

ኮለኔል ጌታቸው ÷ እኛ እያለን ሃገራችን አትደፈርም በማለት በአንድነት መንፈስ ፣ በቁጭትና በሞራል በመነሳሳት ወኔና ጀግንንት ተላብሳችሁ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላት የሆነውን የሽብርተኛ ቡድን በፅናት ለመፋለምና ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም የሚሰጣችሁን ስልጠና በአግባቡ በመወጣት የጠላትን አንገት በማስደፋት ለወገን መከታ፣ አለኝታና ኩራት መሆን አለባችሁ ብለዋል።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ስልጠና ሃላፊ ኮሎኔል ተዝገራ ከበደ በበኩላቸው÷ በማሰልጠኛ ቆይታችሁ የሚሰጣችሁን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት መሰልጠን ፣ በስልጠናው ሂደት የሚያጋጥማችሁን ጥቃቅን ችግሮች በቆራጥነት ማለፍና በጠንካራ ወታደራዊ ዲስፕሊን ስልጠናውን በማጠናቀቅ ለህዝብና ለሃገር የገባችሁትን ቃል ልታረጋግጡ ይገባልም ነው ያሉት።

አንዳንድ ምልምል ሰልጣኞች በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ለሃገር ሉዓላዊነት ውድ ህይወቱን ከሚሰጠው ጀግና ሰራዊት ጐን ለመቆም ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርቱ በመምጣታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የሚሰጣቸውን ወታደራዊ ስልጠና በቁርጠኝነት ሰልጥነው የሽብርተኛውን ሃይል ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸዉንም ምልምል ሰልጣኞቹ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.