ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል – ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል አሉ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች የሠላም፣ የአንድነት እና የልማት ኮንፈረንስ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በውስጡ 32 ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን አቅፎ በመያዝ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ከለውጡ በፊት የነበሩ የሕዝብ ጥያቄዎች በተደራጀ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ ሰፊ ስራዎች መከናወኑን አንስተው÷ በክልሉ በግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና በሌሎች ዘርፎች ትላልቅ የመልማት አቅም መኖሩን አብራርተዋል።
ኮንፈረንሱ ለክልሉ ሕዝቦች ሠላም፣ አንድነት እና ልማት የጎላ ፋይዳ እንዳለውና በየደረጃው ያሉ ሰዎችን በማሰባሰብ በጋራ አቅምን፣ እውቀትን፣ ጉልበትንና ልምድን በመጠቀም የኢትዮጵያ ማንሰራራት ውስጥ ድርሻ ለመወጣት ያስችላል ብለዋል።
ኮንፈረንሱ የክልሉ እምቅ ሀብት በማውጣት ለሀገረ መንግስት ግንባታ አበርክቶ እንዲኖር እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ ተግዳሮት የሚሆኑ ጉዳዮች በተለይም ፅንፈኝነት፣ በየአካባቢው ያለውን እምቅ አቅም በሚገባ መጠቀም አለመቻልና ምርታማ ያለመሆን ችግሮች በውይይትና ምክክር መፍታት በኢትዮጵያ ብልፅግና እና ማንሰራራት ላይ ትልቅ አሻራ እንደሚያኖረውም አብራርተዋል።
በመለሰ ታደለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!