በበጀት ዓመቱ ሁለት ወራት ከወጪ ንግድ 692 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከሐምሌ እና ነሐሴ ወር ወጪንግድ 692 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት ሁለት ወራት ውስጥ የተገኘው ገቢ ከዕቅድ አንጻር በግብርና ምርት የታቀደው 424 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ሲሆን÷ የተከናወነው ደግሞ 502 ሚሊየን ዶላር ነው ተብሏል፡፡
ይህም የዕቅዱን 118 በመቶ ማሳካቱን የሚያሳይ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም ንግድ እና ኢንዱስትሪ ከሚከታተላቸው ምርቶች 82 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማስገኘት አቅዶ 85 ሚሊየን ዶላር ገቢ በማስገኘት ከዕቅዱ በላይ 104 በመቶ ማሳካቱ ነው የተመላከተው፡፡
በሌላ በኩል የማዕድን ዘርፍ 119 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማሳካት አቅዶ ያሳካው 88 ሚሊየን ዶላር በመሆኑና ይህም የዕቅዱን 74 በመቶ ገቢ ብቻ በመሆኑ ዝቅተኛ አፈጻጸም ተብሎ መመዝገቡ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!