Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 490 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቀን፣ በማታ፣ በርቀት እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ መርሐግብር በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው በዛሬው እለት አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር ገመቹ አራርሳ የምረቃ መርሀግበሩን አስመልክተው ባደርጉት ንግግር፥ ዩኒቨርሲቲው የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ተበሎ ከተቋቋም ከ 1999 አ.ም ጀምሮ የክልሉን የሰው ሃይል ለማጠናከር በትምህርት፣ በምርምርና ስልጥና ፣ በማማከር ስፋፊ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በዘንድሮው አመት ከሶማሌ እና ከጋንቤላ ክልል መጥተው የተማሩ ምሩቃን እንዳሉ የጠቀሱት ፕሬዘዳንቱ ፥ዩኒቨርስቲው ከራሱ ክልል በተጨማሪ ሌሎች ክልሎችንም እያገዘ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.